የሀገር ውስጥ ዜና

በአቶ ደመቀ መኮንን የተመራ ከፍተኛ የልዑካን ቡድን ታንዛኒያ ገባ

By Feven Bishaw

July 24, 2023

 

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 17፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ደመቀ መኮንን የተመራ ከፍተኛ የልዑካን ቡድን ታንዛኒያ ዳሬ ሰላም ገብቷል።

ልዑኩ ጁሊየስ ኔሬሬ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርስ የታንዛኒያ ምክትል የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አምባሳደር ምባሮክ ኤን ምባርክ፣ በታንዛኒያ የኢትዮጵያ አምባሳደር ሽብሩ ማሞ እና ዲፕሎማቶች አቀባበል አድርገውላቸዋል፡፡

ልዑኩ ነገ እና ከነገ በስቲያ በሚካሄደው የአፍሪካ የሰው ሃብት የመሪዎች ጉባኤ ላይ ለመሳተፍ ታንዛኒያ መግባቱን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መረጃ ያመላክታል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/ ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!