አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 17፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በተለያዩ መስኮች የተሰማሩ 20 የቻይና ባለሃብቶች የኢትዮጵያ ምርት ገበያ የስራ እንቅስቃሴን ጎብኝተዋል።
ባለሀብቶቹ የምርት ገበያውን አሰራር አስመልክቶ ከተቋሙ ዋና ዳይሬክተር ወንድማገኘሁ ነገራ ጋር ተወያይተዋል።
አቶ ወንድማገኘሁ በምርት ገበያው ከሚገበያዩ ምርቶች አብዛኞቹ ወደ ቻይና የሚላኩ በመሆናቸው እሴት በሚጨምር መስክ ቢሰማሩ አዋጭ እንደሆነ ገልጸውላቸዋል።
ባለሀብቶቹም ጠቃሚ መረጃ እንዳገኙና ከምርት ገበያው ጋር ተቀራርበው ለመስራት ፍላጎት እንዳላቸው መናገራቸውን የዘገበው ኢዜአ ነው።
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/ ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!