የሀገር ውስጥ ዜና

የጠቅላይ ሚኒስትር ጽ/ቤት እና ተጠሪ ተቋማቱ የክረምት በጎ ፈቃድ ስራ አስጀመሩ

By ዮሐንስ ደርበው

July 25, 2023

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 18፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት እና ተጠሪ ተቋማት ሰራተኞች በሸገር ከተማ ፉሪ ክፍለ ከተማ ገዳ ፋጂ ወረዳ የክረምት በጎ ፈቃድ መርሐ-ግብር አስጀምረዋል።

በመርሐ-ግብሩ የአቅመ ደካሞች ቤት እና የትምህርት ቤት እድሳት እንዲሁም የችግኝ ተከላን ጨምሮ ሌሎች የበጎ ፈቃድ ስራዎች እንደሚከናወኑ መገለጹን ኢዜአ ዘግቧል፡፡