የሀገር ውስጥ ዜና

የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና መሰጠት ጀመረ

By Melaku Gedif

July 26, 2023

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 19፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የ2015 ዓ.ም ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት መልቀቂያ የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና መሰጠት ጀምሯል።

በዛሬው ዕለት የ12ኛ ክፍል የማህበራዊ ሳይንስ ተፈታኝ ተማሪዎች ፈተናቸውን እየወሰዱ መሆኑን የትምህርት ሚኒስቴር አስታውቋል፡፡

የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ የማህበራዊ ሳይንስ ፈተና ከሐምሌ 19 እስከ 21 ቀን 2015 ዓ.ም እንደሚሰጥ ታውቃል፡፡