የሀገር ውስጥ ዜና

የእንጀራ ልጆቿን በአሰቃቂ ሁኔታ የገደለችው ግለሰብ የሞት ቅጣት ተፈረደባት

By Amele Demsew

July 26, 2023

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 19፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በሸገር ከተማ ቡራዩ ክፍለ ከተማ ከታ ወረዳ ሁለት የእንጀራ ልጆቿን በአሰቃቂ ሁኔታ የገደለችው ግለሰብ የሞት ቅጣት ተፈረደባት፡፡

የሸገር ከተማ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ዛሬ በዋለው ችሎት የሁለት አመትና የአስራ ሁለት አመት የእንጀራ ልጆቿን ሆን ብላና ጨለማን ተገን አድርጋ በቀን 27/08/2015 ዓ.ም ከለሊቱ 5:00 በአሰቃቂ ሁኔታ የገደለችው ወ/ሮ ነጋሴ ከበደ በሞት ፍርድ እንድትቀጣ ውሳኔ ማስተላለፉን ኦቢኤን ዘግቧል፡፡

ተከሳሿ ወንጀሉን ፈጽማ ከሸሸችበት እለት አንስቶ በፖሊስ ስትፈለግ ከቆየች በኋላ ፖሊስ ባካሄደው ከፍተኛ ጥረት ግንቦት 1/2015 ዓ.ም በቁጥጥር ስር ውላ የፍርድ ሂደቷን ስትከታተል እንደቆየች ችሎቱ አስረድቷል።