የሀገር ውስጥ ዜና

የቁልቢ ገብርኤል ዓመታዊ ክብረ-በዓል በሰላም ተጠናቀቀ

By ዮሐንስ ደርበው

July 26, 2023

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 19፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የቁልቢ ገብርኤል ዓመታዊ ክብረ-በዓል በሰላም መጠናቀቁን የፀጥታና ደኅንነት የጋራ ግብረ-ኃይል አስታወቀ።

አስተዳደር አካላት፣ የሃይማኖት አባቶች እና የአካባቢው ሕብረተሰብ በቅንጅት በሰሩት የፀጥታ ማስከበር ሥራ በዓሉ በሰላም መጠናቀቁን የፌደራል ፖሊስ መረጃ ያመላክታል፡፡

በዓሉ በሰላም ተከብሮ እንዲጠናቀቅ ከፀጥታ አካላት ጎን ሆነው እገዛ ላደረጉ የሕብረተሰብ ክፍሎችም የጋራ ግብረ ኃይሉ ምስጋና አቅርቧል፡፡

በተመሳሳይ በሐዋሳ የተከበረው ዓመታዊው የቅዱስ ገብርኤል በዓል በሰላም መጠናቀቁን የሲዳማ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር ሽመልስ ቶማስ ተናግረዋል፡፡

በዓሉ ሰላማዊ ሆኖ እንዲጠናቀቅ አስተዋጽኦ ያበረከቱ አካላትንም አመስግነዋል፡፡