የሀገር ውስጥ ዜና

የጣሊያን የሥነ-ምኅዳር ዘላቂነት ሚኒስቴር በኢትዮጵያ ያቋረጣቸውን ፕሮጀክቶች ዳግም ሊጀምር ነው

By Mikias Ayele

July 26, 2023

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 19፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የጣሊያን የሥነ-ምኅዳር ዘላቂነት ሚኒስቴር በኮቪድ -19 ወረርሽኝ ምክንያት በኢትዮጵያ አቋርጧቸው የነበሩ ፕሮጀክቶችን ዳግም ሥራ እንዲጀምሩ ለማድረግ ከስምምነት ደርሷል፡፡

በዓለም የሥርዓተ- ምግብ ጉባዔ እየተሳተፉ ያሉት የኢትዮጵያ የአካባቢ ጥበቃ ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር  ጌታሁን ጋረደው (ዶ/ር) ከመደኛ ስብሰባቸው ጎን ለጎን ከጣሊያን የሥነ-ምኅዳር ዘላቂነት አመራሮች ጋር መክረዋል፡፡

በውይይታቸውም÷ ጣሊያን በኢትዮጵያ የአካባቢ ዘላቂነት እንዲረጋገጥ የምታደርገውን ድጋፍ አጠናክራ  እንድትቀጥል ዋና ዳይሬክተሩ ጠይቀዋል፡፡

የጣሊያን የሥነ-ምኅዳር ዘላቂነት ሚኒስቴር አመራሮችም÷ በኮቪድ- 19 ወረርሽኝ ምክንያት ተቋርጠው የነበሩ ፕሮጀክቶች በአጭር ጊዜ ሥራ እንዲጀምሩ ከስምምነት መድረሳቸውን የባለስልጣኑ መረጃ ያመላክታል፡፡