አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 19፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የአፋር ክልል የ2016 ዓ.ም በጀት ከ11 ቢሊየን 993 ሚሊየን ብር በላይ ሆኖ ጸደቀ፡፡
የአፋር ክልል ምክር ቤት በመደበኛ ጉባዔው የክልሉን የ2016 ዓ.ም በጀት መርምሮ አፅድቋል።
የበጀት እጥረት ችግርን በመቅረፍ ረገድ የገቢ አቅምን ማሳደግና አላስፈላጊ ወጪን መቀነስ እንደሚገባ ርዕሰ መስተዳደር አወል አርባ አሳስበዋል።
ገቢን በተገቢው መንገድ መሰብሰብ ካልተቻለ ፈተናዎችን መሻገር እንደማይቻልም መግለጻቸውን ኢቢሲ ዘግቧል፡፡
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/ ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!