የሀገር ውስጥ ዜና

በሳይንሥ ሙዚየም ሲካሄድ የነበረው ሀገር አቀፍ የጤና አውደ ርዕይ ተጠናቀቀ

By Amele Demsew

July 27, 2023

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 20፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ሰኔ 13 ቀን 2015 ዓ.ም ተከፍቶ ለእይታ ክፍት የሆነው ሀገር አቀፍ የጤና አውደ ርዕይ ከአንድ ወር ቆይታ በኋላ ዛሬ ተጠናቋል።

በዚህ አውደ ርዕይ ላይ ከ250 በላይ ተቋማት አገልግሎታቸውን ለእይታ ማቅረባቸው ተገልጿል፡፡

ይህ ሀገር አቀፍ አውደ ርዕይ የጤናው ዘርፍ አሁን የደረሠበትን ደረጃ ያሳየ ነበር ተብሏል፡፡

ኢትዮጵያ ከአገር በቀል ዕውቀት እስከ አርቴፊሻል ኢንተለጀንስ የሕክምና ቴክኖሎጂዎች የደረሰችበት የዘርፉ ዕድገት በአውደ ርዕዩ ለዕይታ መቅረቡም ተጠቅሷል።

ከአንድ ወር በላይ በቆየው አውደ ርዕይ የመንግስትና የግል የጤና ተቋማት፣ ዩኒቨርሲቲዎችና የዘርፉ የምርምር ድርጅቶች ምርትና አገልግሎቶች እንዲሁም በኢትዮጵያ ለባህል ህክምና የሚያገለግሉ ምርቶች ቀርበዋል።

በሰሎሞን ይታየው