ዓለምአቀፋዊ ዜና

ፕሬዚዳንት ፑቲን የሩሲያ ቋንቋ ትምህርት ቤቶች በአፍሪካ እንዲቋቋሙ ጥሪ አቀረቡ

By Melaku Gedif

July 27, 2023

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 20፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የሩሲያ ፕሬዚዳት ቭላድሚር ፑቲን በአፍሪካ ሀገራት የሩሲያ ቋንቋ ትምህርት ቤቶች እንዲቋቋሙ ጥሪ አቅርበዋል፡፡

ፕሬዚዳንት ፑቲን በሩሲያ እየተካሄደ በሚገኘው 2ኛው የሩሲያ-አፍሪካ የመሪዎች ጉባኤ ላይ÷ ሞስኮ በአፍሪካ የሩሲያ ቋንቋ ትምህርት ቤቶችን የማቋቋም ፍላጎት እንዳላት ተናግረዋል፡፡

የቋንቋ ትምህርት ቤቶቹ በሩሲያ እና በአፍሪካ ሀገራት መካከል ያለውን ሁለንተናዊ ግንኙነት ይበልጥ ለማሳደግ እንደሚያስችሉ አንስተዋል፡፡

ከዚህ ባለፈም ሩሲያ ከአፍሪካ ጋር በመግባባት እና የጋራ ተጠቃሚነትን መሰረት ያደረገ ዘላቂ ግንኙነት እንድትመሰርት ከፍተኛ ሚና እንደሚጫወት ጠቁመዋል፡፡

ስለሆነም ሩሲያ በአፍሪካ ሀገራት የሩሲያ ቋንቋ ትምህርት ቤቶችን ማቋቋም በሚቻልበት ሁኔታ ላይ በትኩረት ትሰራለች ነው ያሉት፡፡

የአፍሪካ ሀገራትም የሩሲያ ቋንቋ ትምህርት ቤቶችን እንዲያቋቁሙ ፕሬዚዳንት ፑቲን ጥሪ ማቅረባቸውን አር ቲ ዘግቧል፡፡