የሀገር ውስጥ ዜና

በቀደምት አርበኞች እግር እንደ መተካታችን እኛ የዚህ ትውልድ አባላትም የአንድነት፣ የሰላምና የብልጽግና ፋና ወጊዎች ነን- ጠ/ሚ ዐቢይ

By Tibebu Kebede

May 05, 2020

አዲስ አበባ፣ ሚያዚያ 27፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በቀደምት አርበኞች እግር እንደ መተካታችን እኛ የዚህ ትውልድ አባላትም የአንድነት፣ የሰላምና የብልጽግና ፋና ወጊዎች ነን ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድ ገለፁ።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድ 79ኛው ዓመት የኢትዮጵያዊያን አርበኞች የድል በዓል አስመልክተው በፌስቡክ ገፃቸው መልእክት አስተላልፈዋል።