የሀገር ውስጥ ዜና

አጀንዳዎችን በማሰባሰብ ሂደት የሚሳተፉ አካላት ተለዩ

By ዮሐንስ ደርበው

July 28, 2023

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 21፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን በክልሎች እና ከተማ አስተዳደሮች ለሚያከናውነው አጀንዳዎችን የማሰባሰብ ስራ የተለያዩ ባለድርሻ አካላትን ለይቷል፡፡

ባለድርሻ አካላትም በኮሚሽኑ በሚቀርብላቸው ጥሪ መሰረት በሚደረገው አጀንዳ የማሰባሰብ ሥራ ንቁ ተሳታፊ እንዲሆኑ ተጠይቋል፡፡

የተለዩት ባለድርሻ አካላትም÷ በየወረዳው ከሚገኙ የማህበረሰብ ክፍሎች የተመረጡ ተወካዮች፣ መምህራን ማህበር፣ ሲቪል ማህበራት፣ የፖለቲካ ፓርቲዎች፣ የአሰሪዎች ማህበራት እና የሰራተኞች ማህበራት ፌዴሬሽን ናቸው፡፡

በተጨማሪም÷ የሐይማኖት ተቋማት፣ የአካል ጉዳተኞች ማህበራት፣ ታዋቂ ሰዎች፣ የሙያ ማህበራት፣ የክልል ምክር ቤት፣ የክልል መንግስት (አስፈፃሚ አካላት) እና የክልል ዳኞች ከተለዩት ባለድርሻ አካላት መካከል ይገኙበታል፡፡

የኮሚሽኑ መረጃ እንዳመላከተው÷ የቀድሞው ሰራዊት ማህበር (የተቀናሽ ሰራዊት ማህበር)፣ የክልል የጋዜጠኞች ማህበር (የሚዲያ ተቋማት ማህበር)፣ የክልል የመንግስት ሰራተኞች፣ የዩኒቨርሲቲ መምህራን፣ የንግድ ማህበራት ምክር ቤት የተለዩ ባለድርሻ አካላት ናቸው፡፡

ከላይ በዝርዝር የተለዩት ባለድርሻ አካላትም በሀገራዊ ምክክር ጉባዔው ላይ የሚፈልጓቸውን አጀንዳዎች እንደሚያቀርቡ ይጠበቃል ብሏል ኮሚሽኑ፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/ ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!