የሀገር ውስጥ ዜና

የ12ኛ ክፍል የማህበራዊ ሳይንስ ብሔራዊ ፈተና ተጠናቀቀ

By Tamrat Bishaw

July 28, 2023

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 21፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ባለፉት ሶስት ቀናት ሲሰጥ የነበረው የ12ኛ ክፍል የማህበራዊ ሳይንስ ብሔራዊ ፈተና በሰላምና በስኬት መጠናቀቁን የትምህርት ምዘና እና ፈተናዎች አገልግሎት አስታውቋል፡፡

የትምህርት ምዘና እና ፈተናዎች አገልግሎት በሂደቱ ለተሳተፉ ሁሉ ምስጋና አቅርቧል፡፡

የተፈጥሮ ሳይንስ ተፈታኞች ቅዳሜና እሁድ ወደ መፈተኛ ማዕከል (ዩኒቨርሲቲ) እንደሚገቡ እና መጪ ሰኞ ደግሞ ገለጻ (ኦሬንቴሽን) እደሚሰጣቸው ተጠቁሟል፡፡

ፈተናቸውን ከማክሰኞ ጀምሮ እስከ አርብ ድረስ እንደሚወስዱም ከአገልግሎቱ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡