አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 22፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የጋምቤላ ክልል ምክር ቤት ለክልሉ መንግስት ለ2016 ዓ.ም የቀረበውን የ5 ነጥብ 3 ቢሊየን ብር በላይ በጀት አጽድቋል።
ምክር ቤቱ ለሁለት ቀናት ሲያካሄደው የቆየውን አራተኛ መደበኛ ጉባኤ ዛሬ አጠናቋል።
ምክር ቤቱ ለአዲሱ በጀት የልማት እና መልካም አስተዳደር እቅድ ማስፈጸሚያ የቀረበለትን 5 ቢሊየን 330 ሚሊየን ብር በጀት አፅድቋል።
ከፀደቀው በጀት መካከል 2 ቢሊየን 367 ሚሊየን ከክልል የተለያዩ የገቢ ምንጮች እንዲሁም ቀሪው 2 ቢሊየን 963 ሚሊየን ብር ደግሞ ከፌደራል መንግስት በድጎማና ሌሎች አማራጮች የሚሸፈን መሆኑ እንደተገለጸ ኢዜአ ዘግቧል።
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/ ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!