የሀገር ውስጥ ዜና

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በቦሌ ክ/ከተማ የሚገኙ የከተማ ግብርና ሼዶችን ጎበኙ

By Amele Demsew

July 29, 2023

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 22፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ዛሬ ከሰዓት በኋላ በአዲስ አበባ ቦሌ ክፍለ ከተማ የሚገኙ የከተማ ግብርና ሼዶችን ጎብኝተዋል።

የከተማ ግብርና በከተሞች ውስጥ አመጋገብ እና ገቢን ለማሻሻል አንዱ መንገድ እንዲሆን ተጠናክሮ እንደሚሰራ መገለጹን የጠቅላይ ሚኒስትር ጽ/ ቤት መረጃ ያመላክታል፡፡