የሀገር ውስጥ ዜና

በትግራይ ክልል አስቸኳይ የሰብዓዊ ዕርዳታ እየቀረበ መሆኑን የክልሉ ጊዜያዊ አስተዳደር ገለጸ

By ዮሐንስ ደርበው

July 30, 2023

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 23፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የፌደራል መንግሥት በትግራይ ክልል አስቸኳይ የሰብዓዊ ዕርዳታ ለሚያስፈልጋቸው ወገኖች የምግብ ድጋፍ እያቀረበ መሆኑን የክልሉ ጊዜያዊ አስተዳደር አደጋ ስጋት አመራር ኮሚሽን አስታወቀ።

የኮሚሽኑ የቅድመ ዝግጅትና አስቸኳይ ግብረ-መልስ ዳይሬክተር ገ/እግዚአብሔር አረጋዊ እንዳሉት÷ ወደ ክልሉ የተላከው የምግብ እህል ድጋፉ ለሚያስፈልጋቸው በ17 ወረዳዎች ለሚገኙ ሰዎች ከትናንት ጀምሮ ተደራሽ እየተደረገ ነው፡፡

ድጋፉ ሩዝን ጨምሮ 28 ሺህ 132 ኩንታል የምግብ እህል እና 47 ሺህ 120 ሊትር የምግብ ዘይትን ያካተተ መሆኑን ለኢዜአ ተናግረዋል፡፡

እስከዚህ ወር መጨረሻም ድጋፉ ለሚያስፈልጋቸው ወገኖች መከፋፈሉ እንደሚቀጥል ጠቁመዋል፡፡

#Ethiopia

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/ ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!