የሀገር ውስጥ ዜና

ከ454 ሚሊየን ብር በላይ ዋጋ ያላቸው የኮንትሮባንድ ዕቃዎች ተያዙ

By ዮሐንስ ደርበው

July 31, 2023

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 24፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በተለያዩ ቅርንጫፍ ጽ/ቤቶች አማካኝነት ከ454 ሚሊየን ብር በላይ ዋጋ ያላቸው የኮንትሮባንድ ዕቃዎች መያዙን የጉምሩክ ኮሚሽን አስታወቀ፡፡

በተጨማሪም የኮንትሮባንድ ዕቃዎቹን ሲያዘዋውሩ የተገኙ 11 ግለሰቦችና 4 ተሽከርካሪዎች በቁጥጥር ስር ውለዋል ተብሏል፡፡

ኮሚሽኑ ከሐምሌ 14 እስከ 20 ቀን 2015 ዓ.ም ባደረገው ክትትል÷ 194 ሚሊየን የገቢ እና ከ260 ሚሊየን ብር በላይ ዋጋ ያላቸው  የወጪ ኮንትሮባንድ ዕቃዎች መያዙን ገልጿል፡፡

ከተያዙት ዕቃዎች መካከል÷ አልባሳት፣ ነዳጅ፣ የቁም እንስሳት፣ ኤሌክትሮኒክስ፣ ቡና፣ መድኃኒት፣ የመዋቢያ ዕቃዎች፣ የጦር መሳሪያዎች፣ ጫት፣ አደንዛዥ እጾች፣ የምግብ ዘይት እና የተለያዩ ሀገር ገንዘቦች ይገኙበታል፡፡

የኮንትሮባንድ ዕቃዎቹ በፍተሻ፣ በበረራና በጥቆማ መያዛቸውን የኮሚሽኑ መረጃ ያመላክታል፡፡

#Ethiopia