አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 24፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የአዲስ አበባ ፍትህ ቢሮ መንግስታዊና መንግስታዊ ካልሆኑ ድርጅቶች ጋር ህገ-ወጥ የሰዎች ዝውውርን በጋራ ለመከላከል የሚያስችለውን የመግባቢያ ስምምነት ተፈራረመ።
ስምምነቱን የአዲስ አበባ ፍትህ ቢሮ ኃላፊ ተክሌ በዛብህ ከ22 ተቋማት ኃላፊዎች ጋር ነው የተፈራረሙት።
ዓላማውም ህገ-ወጥ የሰዎች ዝውውርን ለመከላከል የተሻለ ቅንጅታዊ አሰራር እንዲኖር እንዲሁም ለተጎጂዎች የሚሰጡ አገልግሎቶች በተሻለ አግባብ ማቅረብ ይቻል ዘንድ ነው ተብሏል።
አቶ ተክሌ በዛብህ በዚሁ ወቅት እንደተናገሩት ፥ ህገወጥ የሰዎች ዝውውር የሀገራት የደህንነት ስጋት እየሆነ መጥቷል።
በርካታ ወንጀሎች በህገ-ወጥ የሰዎች ዝውውር እንደሚፈጸም ገልጸው ፥ ይህንን ለመከላከል በቅንጅት መስራት እንደሚገባ ማስገንዘባቸውን የዘገበው ኢዜአ ነው።
እስካሁን መንግስታዊና መንግስታዊ ያልሆኑ ተቋማት ዘርፈ ብዙ ስራዎች መስራታቸውን ሲናገሩ ፥ አሁንም ከወትሮው የተለየ ቅንጅት እንደሚያስፈልግ ጠቁመዋል።
ዛሬ ከ22 ድርጅቶች ጋር የተደረገው ስምምነት በዘርፉ የሚደረጉ እንቅስቃሴዎች እንዲጠናከሩ እንደሚያግዝም ነው የተናገሩት።
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/ ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!