የሀገር ውስጥ ዜና

የጃፓኑ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ኢትዮጵያን ሊጎበኙ ነው

By Feven Bishaw

July 31, 2023

 

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 24፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ)የጃፓኑ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሀያሺ ዮሺማሳ ኢትዮጵያን ሊጎበኙ መሆኑ ተገለፀ፡፡

የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ የአፍሪካ ጉብኝታቸውን ዛሬ ጀምረዋል፡፡

ሚኒስትሩ ደቡብ አፍሪካን እና ኡጋንዳን ከጎበኙ በኋላም ወደ ኢትዮጵያ በመምጣት ጉብኝት እንደሚያደርጉ ነው የተገለፀው፡፡

በኢትዮጵያ ቆይታቸው ከከፍተኛ የመንግስት የስራ ሃላፊዎች ጋር እንደሚመክሩ ይጠበቃል፡፡