የሀገር ውስጥ ዜና

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር) ከዓለም ባንክ ፕሬዚዳንት ጋር የቦሌ ለሚ ኢንዱስትሪ ፓርክን ጎበኙ

By Feven Bishaw

August 01, 2023

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 25፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከዓለም ባንክ ፕሬዚዳንት አጃይ ባንጋ ጋር በመሆን የቦሌ ለሚ 2 ኢንዱስትሪ ጎበኙ።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በዓለም ባንክ ድጋፍ የተገነባውን የቦሌ ለሚ 2 ኢንዱስትሪ ፓርክ አጠቃላይ የሥራ እንቅስቃሴና እያከናወናቸው ያሉ ተግባራትን ለፕሬዚዳንቱ አስጎብኝተዋቸዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በፓርኩ ውስጥ ከፕሬዚዳንቱ ጋር በመሆንም ችግኝ መትከላቸውን ኢፕድ ዘግቧል።

የባንኩ ፕሬዚዳንት ትናንት አዲስ አበባ መግባታቸው የሚታወስ ሲሆን÷ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) ፕሬዚዳንቱን በጽሕፈት ቤታቸው ተቀብለው አነጋግረዋል፡፡