የሀገር ውስጥ ዜና

ብርሃኑ ነጋ (ፕ/ር) የ12ኛ ክፍል የተፈጥሮ ሳይንስ ፈተና ሒደትን ጎበኙ

By Amele Demsew

August 01, 2023

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 25፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የትምህርት ሚኒስትር ብርሃኑ ነጋ (ፕ/ር) በተለያዩ ዩኒቨርሲቲዎች የ12ኛ ክፍል የተፈጥሮ ሳይንስ የፈተና አሠጣጥ ሒደትን ተዘዋውረው ተመልክተዋል።

ሚኒስትሩ በአዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ፣ በሲቪል ሠርቪስ ዩኒቨርሲቲ እና በፌዴራል ቴክኒክና ሙያ ትምህርት ኢንስቲትዩት የሚፈተኑ ተማሪዎችን ጎብኝተዋል፡፡

በምልከታቸውም÷ ሁለተኛው ዙር የተፈጥሮ ሳይንስ የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ብሄራዊ ፈተና በጥሩ ሁኔታ እየተሠጠ መሆኑን ገልጸዋል፡፡

ዛሬ የተጀመረው የተፈጥሮ ሳይንስ ፈተና እስከ ሐምሌ 28 ቀን 2015 ዓ.ም ለተከታታይ አራት ቀናት ይሰጣል።

የመጀመሪያው ዙር የማህበራዊ ሳይንስ ፈተና ሚስጥራዊነቱና ደህንነቱ በተጠበቀ መልኩ መጠናቀቁ ንም የሚኒስቴሩ መረጃ አስተውሷል፡፡