የሀገር ውስጥ ዜና

በሸገር ከተማ በደረሰ የትራፊክ አደጋ የ6 ሰዎች ሕይወት አለፈ

By ዮሐንስ ደርበው

August 01, 2023

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 25፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በሸገር ከተማ አስተዳደር ገፈርሳ ጉጄ ክፍለ ከተማ ገፈርሳ አካባቢ በደረሰ የትራፊክ አደጋ የስድስት ሰዎች ሕይወት ማለፉን ፖሊስ አስታወቀ፡፡

በተጨማሪም በዘጠኝ ሰዎች ላይ ከባድ እና ቀላል የአካል ጉዳት መድረሱን የክፍለ ከተማው ፖሊስ መምሪያ የትራፊክ ደኅንነት ዲቪዥን ረዳት ኢንስፔክተር ጉዲሳ ተሬሳ ተናግረዋል፡፡

አደጋው የደረሰው ዛሬ ከቀኑ 6፡00 አካባቢ መሆኑንም ነው ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት የገለጹት፡፡

የግንባታ ቁሶችን ጭኖ ከቡራዩ ወደ ኬላ ሲጓዝ የነበረ ተሽከርካሪ በተቃራኒ መስመር ይጓዝ ከነበረ መለስተኛ የሕዝብ ማመላለሽ ተሽከርካሪ ጋር በማጋጨታቸው ነው አደጋው የተከሰተው ብለዋል፡፡

በሲፈን መገርሳ

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/ ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!