አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 25፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በደብረ ብርሃን ከተማ ለሚገኙ ተፈናቃዮች 20 ሚሊየን ብር ዋጋ ያለው ምግብ ነክ እና ሌሎች ቁሶች ድጋፍ ተደረገ፡፡
በከተማዋ በተለያዩ የመጠለያ ጣቢያዎች ለሚገኙ ወገኖች ድጋፍ ያደረገው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋኅዶ የልማት ክርስቲያናዊ ተራድዖ ኮሚሽን ነው፡፡
የኮሚሽኑ ኮሚሽነር ይልቃል ሽፈራው ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት እንደገለጹት÷ ድጋፉ ከኖርዌይ ቤተክርስቲያን የዕርዳታ እና ኦቻ የልማት ድርጅቶች ጋር በመተባበር የቀረበ ነው፡፡
በዚህም ዛሬ የመጀመሪያው ዙር ከ20 ሚሊየን ብር በላይ ግምት ያላቸው ምግብ ነክና ሌሎች ቁሶች ድጋፍ ቀርቧል ነው ያሉት፡፡
ተፈናቃዮቹ እስከሚቋቋሙ ድረስም የልማት ድርጅቱ ከዜጎች ጎን እንደሚቆም አረጋግጠዋል፡፡
በታለ ማሞ
#Ethiopia
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/ ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!