የሀገር ውስጥ ዜና

የመከላከያ ሠራዊት ላይ የሚሰነዘረው ስም ማጠልሸት እንዲቆም ማስጠንቀቂያ ተሰጠ

By Meseret Awoke

August 01, 2023

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 25፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የሀገር ጠባቂ በሆነው መከላከያ ሠራዊት ላይ የሚሰነዘረው ስም የማጠልሸት ተግባር እንዲቆም ሲል የኢፌዲሪ መከላከያ ሠራዊት አስጠነቀቀ።

አሁናዊ የሰራዊቱ ተግባር ላይ መግለጫ በዛሬው ዕለት ተሰጥቷል፡፡

የኢፌዴሪ ሀገር መከላከያ ሰራዊት የህዝብ ግንኙነት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ኮሎኔል ጌትነት አዳነ በመግለጫቸው ፥ ሠራዊቱ በህዝብና በመንግስት የተሰጠውን ሃላፊነት እየተወጣ ነው ብለዋል።

ሠራዊቱ በኦሮሚያ ክልል በሚንቀሳቀሰው አሸባሪው ሸኔና በአማራ ክልል በፋኖ ስም በሚንቀሳቀሱ የታጠቁ አካላት ላይ እርምጃ እየወሰደ ነውም ተብሏል።

ከሁለቱም ክልሎች ለታጠቁ አካላት የቀረበውን የሰላም ጥሪ ሠራዊቱ ያከብራል ያሉት ኮሎኔል ጌትነት፥ በዚህም የሰላም ጥሪ የተቀበሉ የታጠቁ አካላት ሰላማዊ መንገድን መርጠዋል ብለዋል።

በአዳነች አበበ

#Ethiopia

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/ ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!