የሀገር ውስጥ ዜና

መቀሌ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎችን መቀበል ጀመረ

By Melaku Gedif

August 02, 2023

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 26፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) መቀሌ ዩኒቨርሲቲ በዛሬው ዕለት ተማሪዎችን መቀበል መጀመሩን የትምህርት ሚኒስቴር አስታውቋል፡፡

በሚኒስቴሩ የአስተዳደርና መሰረት ልማት ዋና ስራ አስፈጻሚ ሰለሞን አብርሃ (ዶ/ር)÷ መቀሌ ዩኒቨርሲቲ በዛሬው ዕለት ተማሪዎችን መቀበል መጀመሩን አረጋግጠዋል፡፡

በዛሬው ዕለት የሚገቡትም ዩኒቨርሲቲው  የመማር ማስተማር ሒደቱን ባቋረጠበት ዓመት ላይ ተመራቂ የነበሩ ተማሪዎችን መሆናቸውን  ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት  ተናግረዋል፡፡

በሰሜኑ የኢትዮጵያ ክፍል በነበረው ግጭት ሳቢያ በመቀሌ ዩኒቨርሲቲ የመማር ማስተማር ሒደቱ ተቋርጦ መቆየቱ ይታወሳል፡፡

 

በመላኩ ገደፍ