የሀገር ውስጥ ዜና

የዓለም ባንክ ፕሬዚዳንት በጥቃቅንና መካከለኛ ኢንዱስትሪ የተሰማሩ ሴት አምራቾችን ጎበኙ

By Tamrat Bishaw

August 02, 2023

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 26፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የዓለም ባንክ ፕሬዚዳንት አጀይ ባንጋ በሁለተኛው ቀን የኢትዮጵያ ቆይታቸው በጥቃቅንና መካከለኛ ኢንደዱስትሪ የተሰማሩ ሴት አምራቾችን ጎብኝተዋል።

በኢትዮጵያ መንግስትና የዓለም ባንክ ድጋፍ በሚንቀሳቀሰው የሴቶች ኢንተርፕሩነር ሺፕ ልማት ፕሮግራም ተጠቃሚ የሆኑ ሴቶችን በማምረቻ ቦታቸው በመገኘትም አነጋግረዋል።

በጉብኝታቸው በጫማ ምርት ላይ የተሰማራውን የምስጋና ጫማ ማምረቻን የጎበኙ ሲሆን÷ በተመለከቱት ነገር እንደተደነቁ ገልፀዋል።

በርካታ ወጣት ሴቶች ባገኙት ድጋፍ ለብዙዎች የስራ እድል መፍጠራቸውን በማንሳት÷ ይህን እድል ለበርካቶች መፍጠር ቢቻል ብዙ ስራ ፈጣሪዎችን ማፍራት እንደሚቻል ማየታቸውንም አንስተዋል።

ወጣት ስራ ፈጣሪዎች የፋይናንስ ድጋፍ ቢያገኙ ብዙ መስራት እንደሚችሉና ኢትዮጵያ ኢኮኖሚዋን ማሳደግ ት የሚችል በርካታ የሰው ሃይል ያላት መሆኑን ማየታቸውን ፕሬዝዳንቱ ጠቅሰዋል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/ ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!