አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 26፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የክልሉን ወቅታዊ የፀጥታ ሁኔታ በማስመልከት በካቢኔ አባላቱ ተጥሎ የነበረው የሰዓት እላፊ ገደብ አመሻሹ ላይ በተካሄደ አስቸኳይ ስብሰባ ማሻሻያ ተደርጎበታል፡፡
በክልሉ በተከሰተው የፀጥታ ችግር ምክንያት ከምሽቱ 1፡00 ጀምሮ እስከ ንጋቱ 12፡00 ላልተወሰነ ጊዜ የሚተገበር የሰዓት እላፊ ገደብ መጣሉ ይታወሳል።
በመሆኑም የክልሉ ካቢኔ የፀጥታ ሁኔታው እየተሻሻለ መምጣቱን በማስመልከት የሰውና ተሽከርካሪን እንቅስቃሴ የሰዓት ማሻሻያ ማድረጉን አስታውቋል።
በዚህም መሰረት የባለ ሁለትና ባለሶስት እግር ተሸከርካሪ (ባጃጅ) እና የሞተር ተሽከርካሪዎች ከጠዋቱ 12፡00 ጀምሮ እስከ ምሽቱ 12:30 እንዲሰሩ ማሻሻያ ተደርጓል፡፡
የሰዎችን እንቅስቃሴ በሚመለከትም እስከ ምሽት 3፡00 ድረስ መንቀሳቀስ እንደሚቻል መወሰኑን የክልሉ መንግስት ኮሙኒኬሽን ቢሮ መረጃ ያመላክታል፡፡
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/ ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!