አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 27፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) እንደሀገር ፍትሃዊና ውድድርን ማዕከል ያደረገ የንግድ ትስስር ለመፍጠር እየተሰራ መሆኑን የንግድና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስቴር አስታወቀ።
የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስትር ገብረመስቀል ጫላ ፥ በተጠናቀቀው በጀት ዓመት በተከናወነው የወጪ ንግድ 3 ነጥብ 64 ቢሊየን ዶላር ገቢ መገኘቱን ተናግረዋል፡፡
ከተገኘው ገቢ ውስጥ 79 በመቶ የሚሆነው ድርሻ የግብርናው ዘርፍ መሆኑን ነው ሚኒስትሩ ያብራሩት፡፡
አፈጻጸሙ ከአምናው አንጻር ሲታይ የ487 ሚሊየን ዶላር ቅናሽ ማሳየቱን ጠቁመው፥ለዚህ ምክንያቱ የዓለም ገበያ መቀዛቀዝ፣ የኮንትሮባንድ ንግድና ምርቶችን በወቅቱ ያለማቅረብ ችግሮች መሆናቸውን አስረድተዋል።
በዘርፉ እየተስተዋለ ያለውን የአሰራር ክፍተት በፖሊሲ ደረጃ በማየት ማስተካከል እንዲቻል የተለያዩ አዋጆችና ደንቦች መዘጋጀታቸውንም ነው የተናገሩት።
የኑሮ ውድነቱን ለማረጋጋት የተጀመረው የሰንበት ገበያ ሥርዓት እና በሁሉም አካባቢ ከባለ ድርሻ አካላት ጋር የሚከናወነው ተግባር ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ማንሳታቸውን ኢዜአ ዘግቧል።
#Ethiopia
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/ ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!