የሀገር ውስጥ ዜና

አቪዬሽን አካዳሚ ያሰለጠናቸውን 1 ሺህ 551 ተማሪዎች አስመረቀ

By Amare Asrat

August 05, 2023

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 29፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ አየር መንገድ በአቪዬሽን አካዳሚ ለሦስት ዓመታት ያሰለጠናቸውን ተማሪዎች አስመረቀ።

 

ተመራቂዎቹ 891 ሴት እና 660 ወንድ ሲሆኑ በአጠቃላይ 1 ሺህ 551 ናቸው።

 

ከተመራቂዎቹ ውስጥ ከኢትዮጵያ በተጨማሪ ከሌሎች የአፍሪካ ሀገራት የመጡ ተማሪዎችም ይገኙበታል።

 

አካዳሚዉ በዛሬው ዕለት ያስመረቃቸው አብራሪዎች፣ ቴክኒሻኖች ፣ የበረራ አስተናጋጅ፣ የማርኬቲንግ ባለሙያዎች እና የምግብ ዝግጅት ባለሙያ መሆናቸው ታውቋል።

 

በምረቃ ስነስርዓቱ ላይ የአየር መንገዱ ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ መስፍን ጣሰው ተገኝተዋል።

 

በምንተስኖት ሙሉጌታ