የሀገር ውስጥ ዜና

ዓዲግራት ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎችን መቀበል ጀመረ

By Amare Asrat

August 05, 2023

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 29፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ዓዲግራት ዩኒቨርሲቲ ሁሉንም የመደበኛና የድህረ ምረቃ ተማሪዎች ከዛሬ ሐምሌ 29 ቀን 2015 ዓ.ም ጀምሮ እየተቀበለ እንደሚገኝ አስታወቀ።

በሰሜኑ የሀገራችን ክፍል ተከስቶ በነበረው ግጭት ምክንያት ለሁለት ዓመት የመማር ማስተማር ስራውን ኣቋርጦ የነበረው ዩኒቨርሲቲው፤ መሰረታዊ ጥገናዎችን በማድረግ ተማሪዎችን መቀበል መጀመሩን ገልጿል።

በሚቀጥለው ማክሰኞ የዩኒቨርሲቲው ቦርድ ኣባላት፣ የዩኒቨርሲቲው ማሕበረሰብ አባላት እንዲሁም ሌሎች የህብረተሰብ ክፍሎች በተገኙበት ይፋዊ የአቀባበል ስነ-ስርዓት እንደሚካሄድ ከዩኒቨርሲቲው ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።