አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 29፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የቀድሞው የፓኪስታን ጠቅላይ ሚኒስትር ኢምራን ካሃን ከሙስና ወንጀል ጋር በተያያዘ የሦስት ዓመት እስራት ተፈርዶባቸዋል፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትሩ በቢሯቸው ውስጥ የተቀበሏቸውን ስጦታዎች በመሸጥ የተገኘውን ገንዘብ ባለማሳወቃቸው ጥፋተኛ ተብለው ውሳኔው ተላልፎባቸዋል፡፡
ኢምራን ካሃን ውሳኔውን እንደማይቀበሉት እና ይግባኝ እንደሚጠይቁ ቢያሳውቁም በዛሬው እለት ከመኖሪያ ቤታቸው ተይዘው መታሰራቸው ተሰምቷል፡፡
ከፍርድቤቱ ውሳኔ በኋላ የቀድሞው ጠቅላይ ሚኒስትር በሀገር አቀፍ ደረጃ ተቃውሞ እንዲካሄድ ጥሪ ማቅረባቸው ነው የተገለፀው፡፡
የ70 አመቱ ኢምራን ካሃን በ2018 በፓኪስታን በተደረገው ምርጫ አሸንፈው ሀገሪቱን ለ4 አመታት መምራታቸው የሚታወስ ነው፡፡
ኢምራን ካሃን ከስልጣን ከወረዱ በኋላ ከ100 በላይ ክሶች የቀረቡባቸው ሲሆን÷ ክሶቹ ፖለቲካዊ አንድምታ አላቸው መባሉን ቢቢሲ ዘግቧል፡፡