አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 29፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በ2015/16 የምርት ዘመን በአኩሪ አተር ልማት አዲስ ኢኒሼቲቭ 600ሺህ ሄክታር ለመሸፈን እየተሰራ መሆኑን የኦሮሚያ ክልል ርእሰ መስተዳድር ሽመልስ አብዲሳ ገለፁ፡፡
ርእሰ መስተዳድሩ በማህበራዊ ትስስር ገፃቸው ÷”የኦሮሚያ ክልላዊ መንግሥት የተለያዩ ኢኒሼቲቮችን በመንደፍ ግብርናችንን በሁሉም ዘርፍ ለመቀየር በትጋት እየሰራ ነው” ብለዋል።
በዚህም በ2015/16 የምርት ዘመን በአኩሪ አተር ልማት አዲስ ኢኒሼቲቭ 600 ሺህ ሄክታር ለመሸፈን እየሰራን ነው ያሉ ሲሆን ÷አሁን ላይ ከ470ሺህ ሄክታር በላይ በሰብል መሸፈኑን ገልፀዋል፡፡
አኩሪ አተር በአለም አቀፍ ገበያው ተፈላጊ ከሆኑ ምርቶች አንዱ መሆኑን ያነሱት ርእሰ መስተዳድሩ በትጋት በመስራት፤ ምርቱን በማስፋፋት የግብርናው ሴክተር ለውጭ ገበያ የሚቀርቡ ምርቶችን ለማሳደግ ለያዘው ግብ ከፍ ያለ ድርሻውን እንደሚወጣ ይታመናል ብለዋል።