አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 30፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል በተያዘው የመኸር ወቅት እስካሁን 738 ሺህ 859 ሄታክር መሬት በዘር መሸፈኑን የክልሉ ግብርና ቢሮ አስታውቋል፡፡
የቢሮው ሃላፊ አቶ ባበክር ኻሊፋ እንደገለጹት፥ በተያዘው የመኸር እርሻ 937 ሺህ 722 ሄክታር መሬት በዘር ለመሸፈን ዕቅድ ተይዞ እየተሰራ ነው፡፡
እስካሁን 842 ሺህ 654 ሄክታር መሬት መታረሱን ጠቁመው÷ ከዚህ ውስጥም 738 ሺህ 859 ሄክታር የሚሆነው በዘር መሸፈኑን ተናግረዋል፡፡
የአፈር ማዳበሪያን ጨምሮ ለአርሶ አደሩ አስፈላጊ የሆኑ ግብዓቶች መሰራጨታቸውንም አንስተዋል፡፡
የተዘሩ ሰብሎች ምርታማነታቸው እንዲጨምር የግብርና ባለሙያዎች ለአርሶ አደሩ አስፈላጊውን ድጋፍ እንደሚያደርጉም አስገንዝበዋል፡፡
በመላኩ ገድፍ