አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 1፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የደቡብ ሱዳን ፕሬዚዳንት ሳልቫ ኪር ማያርዲትን ዛሬ ረፋድ ላይ ተቀብለዋል።
በጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት በተካሄደው ስብሰባ ወቅትም መሪዎቹ በሁለትዮሽ ጉዳዮች፣ በንግድ እና በመሰረተ ልማት ዝርጋታ ላይ መክረዋል፡፡
ከዚህ ባለፈም በቀጠናው ሰላምና ጸጥታ ጉዳዮች ላይ መወያየታቸውን የጠቅላይ ሚኒስትር ጽ/ቤት መረጃ ያመላክታል፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር) ”የጋራ ቀጠናዊ ጥቅም ያለን ጎረቤቶች እንደመሆናችን መጠን ትብብራችንን ያለማቋረጥ እናጠናክራለን” ብለዋል፡፡
ፕሬዚዳንት ሳልቫ ኪር ማያርዲት ለአንድ ቀን ይፋዊ የስራ ጉብኝት ነው በዛሬው ዕለት አዲስ አበባ የገቡት፡፡