የሀገር ውስጥ ዜና

አቶ ሙስጠፌ ከዩኤስኤይድ የኢትዮጵያ ተወካይ  ጋር ተወያዩ

By Melaku Gedif

August 09, 2023

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 3፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የሶማሌ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ሙስጠፌ መሃመድ በአሜሪካ ዓለም አቀፍ ተራድኦ ድርጅት (ዩኤስኤይድ) የኢትዮጵያ ተወካይ እስኮት ሆክላደር  ከተመራ  ልዑካን ቡድን ጋር ተወያይተዋል፡፡

በውይይታቸውም÷ በክልሉ መንግስት እና በአሜሪካ ዓለም አቀፍ ተራድኦ ድርጅት መካከል ያለውን ግንኙነት ማጠናከር በሚቻልበት ሁኔታ ላይ መክረዋል፡፡

ከዚህ ባለፈም በተለያዩ  የልማት ፕሮጀክቶች ላይ ያላቸውን ትብብር ለማሳደግ  መወያየታቸውን የክልሉ ኮሙኒኬሽን መረጃ ያመላክታል፡፡

በክልሉ የምግብ ድጋፍ ለሚያስፈልጋቸው የሕብረተሰብ ክፍሎች ድጋፉ በአግባቡ እንዲደረስ ለማድረግ በጋራ መስራት በሚቻልበት ሁኔታ ላይ መምከራቸውም ተገልጿል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/

ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!