የሀገር ውስጥ ዜና

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር) ከደቡብ ኮሪያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጋር ተወያዩ

By Melaku Gedif

August 09, 2023

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 3፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከደቡብ ኮሪያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ፓርክ ጂን ጋር ተወያይተዋል፡፡

በውይይታቸውም በሀገራቱ የሁለትዮሽ ትብብር፣ በቀጣናዊ እና በዓለም አቀፍ ጉዳዮች ላይ መክረዋል፡፡

በሀገራቱ መካከል ያለውን የንግድ ትሥሥር ማሳደግ በሚቻልበት ሁኔታ ላይ መወያየታቸውንም የጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት መረጃ ያመላክታል።