የሀገር ውስጥ ዜና

የቻይና ባለሃብቶች የጅማ ኢንዱስትሪ ፓርክን እየጎበኙ ነው

By Meseret Awoke

August 09, 2023

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 3፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በኢትዮጵያ የቻይና አምባሳደር ዣኦ ዢዩአን እና የቻይና ባለሀብቶች የጅማ ኢንዱስትሪ ፓርክን እየጎበኙ ይገኛሉ።

የኢንቨስትመንት ኮሚሽነር ለሊሴ ነሜ እና የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን ዋና ስራ አስፈፃሚ አክሊሉ ታደሰ በጅማ ኢንዱስትሪ ፓርክ ኢንቨስት የሚያደርጉ ቻይናውያን ባለሃብቶችን ይዘው ጅማ ከተማ ገብተዋል።

ከጉብኝት መርሐ ግብሩ ባሻገር ባለሃብቶቹ የኢንቨስትመንት ስምምነት የፊርማ ስነ ስርዓት ያከናውናሉ ተብሎ እንደሚጠበቅ ከኮርፖሬሽኑ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/ ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!