አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 3፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በቡና ማቀነባበር ላይ የሚሰማራ ሲ ሲ ኢ ሲ ሲ የተሰኘ የቻይና ኩባንያ በጅማ ኢንዱስትሪ ፓርክ ኢንቨስት ለማድረግ የሚያስቸለውን ስምምነት ዛሬ ፈርሟል፡፡
የኢንቨስትመንት ኮሚሽን ምክትል ኮሚሽነር ዳንኤል ተሬሳና የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን ምክትል ስራ አስፈፃሚ ሽፈራው ሰለሞን ከሲ ሲ ሲ ኢ ሲ ሲ ኩባንያ ተወካዮች ጋር ስምምነቱን ፈርመዋል፡፡
ኩባንያው በጅማ ኢንዱስትሪ ፓርክ ኢንቨስት በማድረግ በአካባቢው በስፋት የሚገኘውን የቡና ምርት ማቀነባበር ላይ ይሰራል መባሉን የኢንዱስትሪ ፓርኮች ኮርፖሬሽን መረጃ ያመላክታል፡፡
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/ ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!