አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 5፣ (ኤፍ ቢ ሲ) በዋናነት ስኳሩ ከተገዛበት ሀገር ውስብስብ አሰራርና ቢሮክራሲ ጋር በተያያዘ ጨረታውን ያሸነፈው ድርጅት ምርቱን ወደ ኢትዮጵያ ማምጣት አለመቻሉን የኢትዮጵያ ስኳር ኢንዱስትሪ ግሩፕ አስታወቀ፡፡
ስኳሩ የተገዛው ከብራዚል ሲሆን ጨረታውን ያሸነፈው ድርጅት ምርቱን በሚፈለገው ጊዜ ማድረስ አለመቻሉን የግሩፑ የሕዝብ ግንኙነትና ተሳትፎ ዋና ክፍል ኃላፊ ረታ ደመቀ ተናግረዋል፡፡
ችግሩን ከግንዛቤ በማስገባት ከሁለት እስከ ሦስት ወራት ባለው ጊዜ ምርቱን ወደ ሀገር ውስጥ ለማስገባት ጥረት እየተደረገ ስለመሆኑም ጠቁመዋል፡፡
ምርቱ በአራት ዙር ወደ ሀገር ውስጥ እንደሚገባ ጠቅሰው፤ የተገዛው የስኳር ምርት መጠን 2 ሚሊየን ኩንታል መሆኑን ተናግረዋል፡፡
ለስኳሩ ግዥ 110 ሚሊየን 400 ሺህ ዶላር መመደቡን ነው ያመላከቱት፡፡
በሀገር አቀፍ ደረጃ ከ7 ነጥብ 5 እስከ 8 ነጥብ 5 ሚሊየን ኩንታል የስኳር ምርት ፍላጎት እንዳለ ይገመታል ነው ያሉት፡፡
በዮሐንስ ደርበው
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/ ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!