የሀገር ውስጥ ዜና

አቶ ደመቀ መኮንን ከሩዋንዳ የውጭ ጉዳይና ዓለም አቀፍ ትብብር ሚኒስትር ጋር ተወያዩ

By Mikias Ayele

August 11, 2023

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 5፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን ከሩዋንዳ የውጭ ጉዳይና ዓለም አቀፍ ትብብር ሚኒስትር ቪንሰንት ቢሩታን ጋር ተወያይተዋል፡፡

በውይይታቸው በሁለቱ ሀገራት መካከል ያለው የሁለትዮሽና የባለ ብዙ ወገን ግንኙነት በሚጠናከርበት ሁኔታ ላይ መምከራቸውን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታውቋል።

ሚኒስትር ቪንሰንት ቢሩታ ቀደም ሲል ከጠቅላይ ሚኒስትር  ዐቢይ አህመድ ጋር መወያየታቸው ይታወሳል።