አዲስ አበባ ፣ ነሐሴ 6 ፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የብላቴ ኮማንዶ እና የአየር ወለድ ማሰልጠኛ ማዕከል የተለያዩ አስቸጋሪ መሰናክሎችን ማለፍን እንዲሁም ፈጥኖ መድረስን ለሚጠይቁ ተልዕኮዎች ጠንካራ ስልጠና የወሰዱ በሺዎች የሚቆጠሩ ኮማንዶዎችን ዛሬ እያስመረቀ ነው።
የምርቃት መርሐግብሩን በማስመልከት ሰልጣኞቹ ያገኙትን ክህሎት በትልቅ የአምሳለ እውን ትርኢት አሳይተዋል።
በመርሐግብሩም ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በሺዎች የሚቆጠሩ ታዳሚዎችን የማስተናገድ አቅም ኖሮት በማሰልጠኛ ማዕከሉ የተገነባውን አምፊ ቴአትር በይፋ ከፍተው በአረንጓዴ ዐሻራ መርሐ ግብር ችግኞችን ተክለዋል።