የሀገር ውስጥ ዜና

በአቡራሞ ወረዳ ለሚገነባ ቤተ-መጻሕፍት የመሠረት ድንጋይ ተቀመጠ

By Tamrat Bishaw

August 12, 2023

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 6፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በቱሪዝም ሚኒስቴርና ተጠሪ ተቋማቱ በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል አቡራሞ ወረዳ ለሚገነባ ቤተ-መጻሕፍት የመሠረት ድንጋይ ተቀምጧል፡፡

የመሠረት ድንጋዩ የተቀመጠው በክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አሻድሊ ሀሰን እና በቱሪዝም ሚኒስትር አምባሳደር ናሲሴ ጫሊ ነው፡፡

በዛሬው ዕለትም ሚኒስቴሩና ተጠሪ ተቋማቱ በዑራ እና አቡራሞ ወረዳዎች ከ300 በላይ ለሚሆኑ የአቅመ ደካማ ቤተሰብ ተማሪዎች የትምህርት መማሪያ ቁስ ድጋፍ አድርገዋል፡፡

ሚኒስቴሩና ተጠሪ ተቋማቱ ያደረጉት ድጋፍ የትምህርት ጥራትን ለማስጠበቅ እንደሚያግዝ አቶ አሻድሊ ተናግረዋል፡፡

ድጋፉ የእርስበርስ መደጋገፍና መተባበርን ስለሚያጠናክር ቀጣይነት እንዲኖረው መጠየቃቸውን የክልሉ ኮሙኒኬሽን ቢሮ መረጃ ያመላክታል፡፡

አምባሳደር ናሲሴ ጫሊ በበኩላቸው÷ በክልሉ የትምህርት ጥራትን ለማስጠበቅ በሚደረገው ጥረት የቱሪዝም ሚኒስቴርና ተጠሪ ተቋማቱ የበኩላቸውን አስተዋጽኦ ያደርጋሉ ብለዋል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/ ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!