የሀገር ውስጥ ዜና

የላፕሴት ፕሮጀክትን ለአገልግሎት ክፍት ለማድረግ ሥራዎችን ማፋጠን እንደሚያስፈልግ ተጠቆመ

By Tamrat Bishaw

August 12, 2023

የትራንስፖርትና ሎጅስቲክስ ሚኒስትር ዓለሙ ስሜ (ዶ/ር) የተመራ ልዑክ በኬንያ የሥራ ጉብኝት እያደረገ ነው፡፡

ዓለሙ ስሜ (ዶ/ር) ከጉብኝቱ ጎን ለጎን ከኬንያ የመንገድና ትራንስፖርት ካቢኔ ጸሐፊ ኦኔሲሙስ ኪፕቹምባ ሙርኮመን ጋር በሁለትዮሽ ሀገራዊ ጉዳዮች ላይ ተወያይተዋል።

በውይይታቸውም÷ የላሙ ፖርት-ደቡብ ሱዳን- ኢትዮጵያ ትራንስፖርት (ላፕሴት) ኮሪደር ልማትን ጨምሮ በቀጣናዊ ጉዳዮች ላይ መምከራቸውን በኬንያ የኢትዮጵያ ኤምባሲ መረጃ ያመላክታል፡፡

በዚሁ ወቅትም ዓለሙ (ዶ/ር) የላፕሴት ፕሮጀክት አጠቃቀምን ማፋጠን አስፈላጊ ስለመሆኑ በአጽንኦት ገልጸዋል፡፡

 

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/ ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!