የሀገር ውስጥ ዜና

ከንቲባ አዳነች ግንባታቸው በመጠናቀቅ ላይ የሚገኙ ግዙፍ የግብርና ምርት የገበያ ማዕከላትን ጎበኙ

By Feven Bishaw

August 13, 2023

 

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 7፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ አዳነች አቤቤ ግንባታቸው በመጠናቀቅ ላይ የሚገኙ ግዙፍ የግብርና ምርት የገበያ ማዕከላትን ጎብኝተዋል፡፡

ከንቲባዋ በኮልፌ ቀራንዮ ክፍለከተማ ቤተል አካባቢ እና በለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ አያት አካባቢ ግንባታቸው በመጠናቀቅ ላይ የሚገኙ ግዙፍ የግብርና ምርት የገበያ ማዕከላት ያሉበትን ሁኔታ ነው የጎበኙት፡፡

ከንቲባ አዳነች በማህበራዊ ትስስር ገፃቸው ÷” በመገንባት ላይ የሚገኙት የግብርና ምርት የገበያ ማዕከላት፣ ምርትን በስፋት ወደ ከተማችን ማስገባት ከማስቻል እና በከተማችን ያለውን ህገወጥ የገበያ ትስስር ሰንሰለት ከማስቀረት በተጨማሪ የኑሮ ጫናን የሚያቃልሉና ለነዋሪዎቻችን ተጨማሪ የስራ እድል የሚፈጥሩ ናቸው”ብለዋል።

ለህዝቡ በተገባው ቃል መሰረት የተጀመሩ ፕሮጀክቶችን አዳዲስ ቴክኖሎጂዎችን ተግባራዊ በማድረግ በተያዘላቸው ጊዜ በጥራት በማጠናቀቅ በቅርብ ቀን ለአገልግሎት ክፍት እንደሚደረጉም ገልፀዋል፡፡