የሀገር ውስጥ ዜና

የኢጋድ የሴቶች የሰላምና ደህንነት ፎረምን በይፋ ወደ ስራ የሚያስገባ ውይይት በናይሮቢ ተጀመረ

By Shambel Mihret

August 15, 2023

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 9፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የምስራቅ አፍሪካ የልማት በይነ መንግስታት ባለስልጣን (ኢጋድ) የሴቶች የሰላምና ደህንነት ፎረምን በይፋ ወደ ስራ የሚያስገባ ውይይት በኬንያ ናይሮቢ መካሄድ ጀምሯል።

በውይይቱ ላይ የኢጋድ ባለስልጣናት፣ የተቋሙ አባል አገራት ተወካዮች፣ የሲቪክ ተቋማትና ሌሎች ባለድርሻ አካላት እየተሳተፉ ነው ተብሏል።

የውይይቱ ዓላማ የኢጋድ የሴቶች የሰላምና ደህንነት ፎረምን በይፋ ወደ ስራ እንዲገባ ማድረግ መሆኑ ተገልጿል።

የፎረሙ ስራ መጀመር ኢጋድ ለስርዓተ ጾታ እኩልነት እና ሴቶችን ማብቃት ላይ ያለውን ቁርጠኝነት የሚያሳይ መሆኑም ተመላክቷል።

ውይይቱ እስከ ነገ እንደሚቆይ እና የፎረሙ መመስረትም ለአንድነት፣ ለውይይት እና ለለውጥ ምቹ ሁኔታ ይፈጥራል ተብሎ እንደታመነበት  መገለጹን ኢዜአ ዘግቧል።