የሀገር ውስጥ ዜና

ፊሊፒንስ ከኢትዮጵያ ጋር ያላትን የንግድ ግንኙነት ለማጠናከር ፍላጎት እንዳላት ገለጸች

By Tamrat Bishaw

August 16, 2023

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 10፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ፊሊፒንስ ከኢትዮጵያ ጋር ያላትን የንግድ ግንኙነት የበለጠ ለማጠናከር ፍላጎት እንዳላት የሀገሪቱ ፕሬዚዳንት ፈርዲናንድ ቦንቦንግ ማርከስ ገለጹ፡፡

በፊሊፒንስ የኢትዮጵያ አምባሳደር ሆነው የተሾሙት አምባሳደር ደሴ ዳልኬ የሹመት ደብዳቤያቸውን ለፊሊፒንስ ፕሬዚዳንት ፈርዲናንድ ቦንቦንግ ማርኮስ ጁኒየር አቅርበዋል።

በዚህ ወቅት አፍሪካ አሁን የምትገኝበት ደረጃ እና እያሳየች ያለው እድገት መላውን ዓለም እያስደመመ እንደሚገኝ ፕሬዚዳንቱ ለአምባሳደር ደሴ ገልፀውላቸዋል፡፡

አምባሳደር ደሴ በበኩላቸው ኢትዮጵያ በምስራቅ አፍሪካ በንግድና ኢንቨስትመንት እምቅ አቅም እንዳላት ያላት እና እያደገ ያለ የኢኮኖሚ ባለቤት መሆኗን ጠቅሰዋል።

መልክአ ምድራዊ አቀማመጧም አፍሪካን ከመካከለኛው ምስራቅ እና ምዕራባውያን ሀገራት ጋር የሚያገናኝ እንደሆነም አንስተዋል።

የፊሊፒንስ ባለሃብቶች በኢትዮጵያ መዋዕለ ንዋያቸውን ቢያፈሱ በአፍሪካ ካለው ገበያ ተጠቃሚ መሆን ይችላሉ ማለታቸውን የሀገሪቱ መገናኛ ብዙሃን ዘግቧል።

ፊሊፒንስ ከኢትዮጵያ ጋር ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት የመሰረተችው በፈረንጆቹ የካቲት 7 ቀን 1977 እንደሆነ ተመላክቷል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/ ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!