የሀገር ውስጥ ዜና

በሶማሌ ክልል ከ476 ሺህ በላይ የመማሪያ መጽሐፍት ታትሟል

By ዮሐንስ ደርበው

August 16, 2023

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 10፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ለ2016 የትምህርት ዘመን ለተማሪዎች ከሚያስፈልጉ 971 ሺህ 102 መጽሐፍት 476 ሺህ 102 ያህሉ መታተማቸውን የሶማሌ ክልል ትምህርት ቢሮ አስታወቀ፡፡

ቀሪው በኅትመት ሂደት ላይ መሆኑን የቢሮው የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ አብዱላሂ ኢልሚ ገልጸዋል፡፡

ለትምህርት ዘመኑ የሚያስፈልጉ መጽሐፍትን ሙሉ በሙሉ ለማሳተም 861 ሚልየን ብር እንደሚያስፈልግ ነው ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት የተናገሩት፡፡

ከመስከረም 1 እስከ 7 ቀን 2016 ዓ.ም በክልሉ በሁሉም አካባቢዎች ትምህርት እንደሚጀመርም ጠቁመዋል፡፡

በትምህርት ዘመኑ በክልሉ 1 ሚሊየን 282 ሺህ 670 ተማሪዎች ይገኛሉ ተብሎ እንደሚጠበቅም አመላክተዋል፡፡

ከማተሚያ ቤቶች አቅምና ቁጥር ጋር በተያያዘ የኅትመት ሥራው በሚፈለገው ልክ አለመሄዱን አንስተዋል፡፡

በዮሐንስ ደርበው

#Ethiopia

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/ ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!