የሀገር ውስጥ ዜና

አምባሳደር ተፈሪ ከዓለም ዓቀፍ የስኳር ድርጅት ዋና ዳይሬክተር ጋር ተወያዩ

By Melaku Gedif

August 16, 2023

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 10፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በብሪታንያ የኢትዮጵያ አምባሳደር ተፈሪ መለሰ ከዓለም ዓቀፍ የስኳር ድርጅት ዋና ዳይሬክተር ጆስ ኦራይቭ ጋር ተወያዩ።

በውይይታቸውም አምባሳደር ተፈሪ በኢትዮጵያ ያለውን የለውጥ ሒደት በተመለከተ ገለጻ አድርገዋል።

በተለይም የስኳር ፋብሪካዎችን ጨምሮ በመንግስት እጅ የሚገኙ የልማት ድርጅቶችን ወደ ግል ለማዞር እየተደረገ ያለውን ጥረት አብራርተዋል።

በዚህም በኢትዮጵያ ያሉትን የስኳር ፋብሪካዎች ወደ ግል ለማዞር የሚደረገውን ጥረት ውጤታማ ለማድረግ የሚያስችሉ ተግባራትን በትብብር ለማከናወን መስማማታቸውን በለንደን የኢትዮጵያ ኤምባሲ መረጃ አመልክቷል።