አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 12፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የቡሄ በዓልን ምክንያት በማድረግ በሚከናወነው የችቦ ማብራት ስነ ስርዓት ርችት መተኮስ ክልክል መሆኑን የአዲስ አበባ ፖሊስ አስታውቋል፡፡
ፖሊስ ጉዳዩን አስመልክቶ ባስተላለፈው መልዕክት÷የከተማዋን ሰላም በዘላቂነት ለማረጋገጥ ከሌሎች የፀጥታ አካላት ጋር በመቀናጀት ውጤታማ ተግባራትን እያከናወነ መሆኑን ገልጿል፡፡
ይህንኑ የፀጥታ ስራ በአግባቡ ለመምራትና ለመቆጣጠር ሲባል እንዲሁም አጋጣሚውን በመጠቀም ሊፈፀሙ የሚችሉ ህገ-ወጥ ድርጊቶችን ለመከላከል በቡሄ በዓል ርችት መተኮስ መከልከሉ ተጠቁሟል፡፡
ሕብረተሰቡም ይህን ተገንዝቦ አስፈላጊውን ትብብር እንዲያደርግ የአዲስ አበባ ፖሊስ ጥሪ አቅርቧል፡፡