የሀገር ውስጥ ዜና

የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ሕገ-መንግስት ፀደቀ

By ዮሐንስ ደርበው

August 18, 2023

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 12፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ማዕከላዊ ኢትዮጵያ በሚል ለሚደራጀው ክልል የተዘጋጀው ሕገ-መንግስት በአብላጫ ድምፅ ፀድቋል።

ነባሩ የደቡብ ብሔር፣ ብሔረሰቦች እና ሕዝቦች ክልልን በአዲስ ማዕከላዊ ኢትዮጵያ በሚል ለማደራጀት የተጠራ 6ኛ ዙር 3ኛ ዓመት የሥራ ዘመን 2ኛ አስቸኳይ ጉባዔ በወልቂጤ ከተማ እየተካሄደ ነው፡፡

ጉባዔው በዛሬው ውሎውም ማሻሻያ ተደርጎበት የተዘጋጀው የነባሩ ክልል ሕገ-መንግስት ለምክርቤቱ አባላት ቀርቦ ውይይት ከተደረገበት በኋላ÷ በ5 ተቃውሞ፣ በ3 ድምፅ ተዓቅቦ በአብላጫ ድምፅ አጽድቋል፡፡

#Ethiopia

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/ ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!